ጋብቻ
ጋብቻ በወንዶችና በሴቶች የሚፈጠር በህግና ማህበራዊ ኑሮ ደንብ የተደገፈ ጥምረት ሲሆን ከሁለቱም ወገን ለሚወለዱ ልጆች ኃላፊነት የሚያክልና በህግ ደንብ፣ ባህልና እምነት ተመረኮዘ የተጋቢዎችን መብትና ግዴታ የሚገልፅ ነው ይለዋል 16ኛው እትም ኢንሳይኮሎፒዲያ ብሪታኒካ፡፡
በ1962 ዓ.ም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የታተመው መጽሐፈ ህግጋት አብይት ደግሞ ጋብቻን ከሁለት አንዱ ዘር ለመተካት ልጅ ለመውለድ በሚገናኙበት ጊዜ ፈቃድን የሚሰጡበትና በዚህ ዓለም ድካምን ለማቅለል አንዱ ለአንዱ የሚያደርጉት በተጋቡት መካከል የሚደረግ መረዳዳት በማለት አስፍሮታል፡፡
ይህ የሚያመለክተን በዓለማችን በአብዛኛው ተቀባይነት ስላለው የአንድ ለአንድ ጋብቻ ነው፡፡
በቦታ፣ በጊዜ አለፍ ሲልም በባህልና እምነት ልዩነት ምክንያት በምድራችን አስገራሚና ለጆሮ የሚቀፍ ግንኙነቶችና የጋብቻ ሥርዓቶች ተከናውነዋል፡፡ አልፎ አልፎም በተግባር ላይ እየዋሉ ናቸው፡፡ ከነኝህም ውስጥ ኢንሴስት (የቤተሰብ ውስጥ ወሲባዊ ግንኑነት)፣ ኤንዶ ጋሚ (የጎሳ ውስጥ ጋብቻ) ኤክሶ ጋሚ (ከጎሳ ውጪ ወይም ከጋብቻ ዝምድና ውጪ ያለ ጋብቻ፣ ፓሊጋሚ (የአንድ ለብዙ ጋብቻ) እ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ይገኛሉ፡፡
ኢንሴስት የሚባለው ግንኙነት
በእናትና ወንድ ልጇ ወይም ደግሞ በአባትና ሴት ልጁ መካከል የሚደረግ ሲሆን ይህ ዓይነቱ ግንኙነት ወይም ጋብቻ በዓለም ደረጃ የተወገዘና የተከለከለ ነው የወንድምና እህት መጋባት ግን በማርሻልና ሃዋይ ደሴቶች በጥንታዊዋ አየር ላንድ በግብፅና በኢንካን ንጉሳዊ ቤተሰቦች ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
ከቤተሰብ ወጣ በማለት ደግሞ ጋብቻ በአንድ ጎሳ ውስጥ የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ ይህ ዓይነቱ በጥንት ጊዜ የታየ የጋብቻ ህግ ኋላ ቀር በሆኑ ከሌላ አካባቢ ጋር መገናኛ መንገዶች አስቸጋሪ በሚሆንበት ጊዜም ሆነ በየአካባቢው ካለ የባህል ተጽዕኖ አሁንም ሲተገበር ይስተዋላል፡፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋም ኤንዶጋሚ ተብሎ ይታወቃል፤፤
ከዚህ በተቃራኒ ያለው ኤክሶጋሚ የሚባለው ሲሆን ጋብቻው የሚፈፀመው በተጋቢዎች የዘር አቆጣጠር በመመርኮዝ ነው፡፡ ይህ የጋብቻ ዓይነት በዘመኑ ሁኔታ ተሻሽሎ እየተሰራበት አለ ለምሳሌም በእንግሊዝ አገር ለሁለተኛ ጊዜ የሚያገባው ሰው የባለቤቱን እህት ወይም ወንድም እንዲያገባ ሕግ ይከለክለዋል፡፡
በኛም መጽሐፍ አብይት ህግጋት ከሥጋ ዘመዶች ጋብቻ ሌላ በጥምቀት ክርስትና ዝምድና የተሳሰሩትን ሳይቀር እንዲጋቡ አይፈቅድም፡፡
ከተፈጥሮ ህግ ውጪ አንድ ዓይነት ፆታዎች ከህግ ተደብቀው ጋብቻን የፈጸሙ ተከስተዋል እነኝህም እንደዚሁ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወገዙና የተጠሉ ናቸው፡፡
ከነዚህም ሌላ በ20ኛው ክፍለ ዘመን እየቀነሰ የመጣው የአንድ ለብዙ ጋብቻ ወይም
ፓሊጋሚ የሚባለው ነው፡፡ ፓሊጋሚ በእስልምና ሃይማኖት ህግጋት ታሪክ የአንድ ለብዙ ጋብቻ ተፈቅዷል፡፡ አሁንም በአንድ የአፍሪካ ማህበረሰቦች ይህ ዓይነቱ ጋብቻ ይፈፀማል፡፡ የአንድ ለአንድ ጋብቻም በአብዛኛው እያሰረፀ በመምጣቱ ፓሊጋሚ አልፎ አልፎ ብቻ ነው የሚታየው ይህ ጋብቻ ምርታማነትን በል ልዩ መንገድ የሚቀንስ ከመሆኑም ሌላ የቤተሰብ አባላት ቁጥር ከቤተሰብ ቁሳዊ ምርት እንዲበልጥ የሚያደርግ በመሆኑ የህዝብ ቁጥር ዕድገትን አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ነገሮች እንደ አንዱ ሊቆጠር ይችላል፡፡
የፖሊጋሚ ነገር ሲነሳ በዘመናችን ጉድ ተሰኘው ቶም ግሪን ይጠቀሳል ቶም ግሪን አምስት ሚስቶች ሲያገባ በግንቦት 11 1983 አዲስ ዘመን ጋዜጣ አድማስ አምድ ያሰፈረው “ከህብረተሰቡ ወግ ባህልና ልማድ አፈንግጦ እንዲሁም ክልክሉንና ውግዙን የቤተዘመድ የእርስ በርስ ጋብቻ ህግ ሽሮ የእንጀራ ልጆች ከነእናት ስለማግባቱ የሰማም ሆነ ያወቀ አልነበረም›› በማለት ነበር፡፡
በመጨረሻም በዘመናችን ውስጥ ተቀባይነት ስላለው የአንድ ለአንድ ጋብቻ ትንሽ ልበል፡፡ የትዳር ምስረታ በተለያየ ቦታ ባለው የኢኮኖሚ ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታ ቢወሰንም የእድሜ ደረጃም ግምት ውስጥ ይገባል፡፡
ቱኒዝያ ቤተሰብን በእቅድ ለመምራት እንዲያስችላት የአንድ ለብዙ ጋብቻን አስቀርታ የጋብቻን እድሜ ለሴቶች 17 ለወንዶች ደግሞ 21 ዓመት እንዲሆን ወስናለች ይላል የህዝብ ቁጥር እድገትና የልማት ጥያቄ በሚል ርዕስ ይዞ ያወጣው መስከረም ቅጽ 9 ቁጥር 35 በ1981 እትሙ፡፡
ጋብቻ ሙሉ በሙሉ ነፃ ምርጫ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ በሰለጠነው ኣለም ፍቅር ከጋብቻ ጋር እየተያያዘ ቢመጣም ለዘመናት ፍቅር ለጋብቻ የሚያንደረድር ሆኖ አልተገኘም፡፡ ለፍቅር ከዚያም ለጋብቻ በሚታጩት ላይ ማህበረሰቡ ትኩረት ያደርግባቸዋል ወንዱ ለጋብቻ የፈቀዳትን (በፍቅር ተዋውቀውም ቢሆንም ለቤተሰቦቿ ሽማግሌ ልኮ ስምምነት ሲጠይቅ የልጅቷ ቤተሰቦችም የሚያጣሩትን አጣርተው እስኪፈቅዱ መቆየትም ነፃ ምርጫ አለመሆኑን ያመለክታል፡፡
በእንግሊዝ አገር ያለው የጋብቻ ህግ ለጋብቻ አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች እንደሚከተለው ተንትኖታል፡፡
<!--[if !supportLists]-->- <!--[endif]-->እያንዳንዲ ወገን ለጋብቻ የደረሰ መሆኑ
<!--[if !supportLists]-->- <!--[endif]-->ለወሲባዊ ተራክቦ ብቻ የሆነና ህመም የሌለበት
<!--[if !supportLists]-->- <!--[endif]-->በዘር ሃረግ ውስጥ ዝምድና አንዳቸው ከሌላቸው ከተረጋገጠ እና በሚመለከተው መስሪያ ቤት የጋብቻው ስርዓት ሲፈፀም ነው፡፡
አውሮፓ ውስጥ ባሉት ማህበረሰቦችና በአሜሪካ ያለው የጋብቻ ህግ (በእንግሊዝ የጋብቻ ህግ ላይ የተመሰረተው) የሮማውያን፣ የካቶሊክ ካኖን ህግ ውጤት ሲሆን በዘመኑ የኢንዱስትሪ ከተሞች ህይወት ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታዎች አኳያ ተሻሽሎ የተቀረፀ ነው፡፡
በቀድሞው ሰብየት ህብረት የሲቪል (ህዝባዊ ጋብቻ በሚመለከተው ክፍል ሲመዘገብ ብቻደ ነው፡፡ ዕውቅናን የሚያገኘው አሁን በየሪፐብሊኩ ባህል ካልተለወጠ የአንድ ለአንድ ጋብቻ በጠበቀ መልክ ይከናወናል፡፡ ጋብቻውም በሁለቱም ወገን በፈቃደኝነት ላይ የተመረኮዘና ተጋቢዎቹም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት፡፡
በጃፓን ጋብቻ ከመከናወኑ በፊት ወንዶች 18 ዓመት ሴቶች ደግሞ 16 ዓመት ሊሞላቸው ይገባል፡፡ ጋብቻ በህግ መደገፍም ተገቢ ነው በቻይናም ጋብቻ በህግ ይፀድቃል፡፡
በሀገራችን ጋብቻ በሶስት ዓይት መንገድ ሲታወቅ እነሱም በማዘጋጃ ቤት የሚመዘገብ ህዝባዊ ጋብቻ በቤተክርስቲያን የሚከናወን የሃይማኖት ጋብቻና በተለይ በየገጠሩ የሚከናወኑ ባህላዊ ጋብቻዎች ናቸው፡፡
ስለጋብቻ ይህን ያህል ካልኩ እስቲ ደግሞ በአንድ ወቅት በአዲስ ዘመን የአድማስ እትም ላይ ወጥቶ የነበረውን ልጋብዛችሁና ልሰናበት